Psalms 134

የሠርክ መዝሙር

መዝሙረ መዓርግ።

1እናንት በሌሊት ቆማችሁ በእግዚአብሔር ቤት የምታገለግሉ፣
የእግዚአብሔር ባሪያዎች ሁላችሁ እግዚአብሔርን ባርኩ።
2በመቅደሱ ውስጥ እጆቻችሁን አንሡ፤
እግዚአብሔርንም ባርኩ።

3ሰማይንና ምድርን የሠራ እግዚአብሔር
ከጽዮን ይባርክህ።
Copyright information for AmhNASV